
ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት የተሠማሩ 22 ማኅበራት ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 561 ነጥብ 5 ቶን የዓሣ ምርት ለአካባቢው እና ማዕከላዊ ገበያ አቅርበዋል።
ግድቡ ከኃይል ማመንጨት ባለፈ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ ኢተቻ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በዓሣ ማምረት ለተሠማሩ ማኅበራትም የማምረቻ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!