
አዲስ አበባ: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የላሊበላ እና አካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በላሊበላ እየተካሔደ ነው።
እያጋጠሙ ባሉ የጸጥታ ችግሮች ከትላንት ማንነቷ ዝቅ ብላ የምትገኘውን የላሊበላ ከተማ ሰላሟን በዘላቂነት በማረጋገጥ ወደ ቀደመ ከፍታዋ መመለስ እንደሚገባ የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ ወንድምነው ወዳይ ተናግረዋል።
ችግሮች ሲከሰቱ ጠባሳ እንዳያሳድሩ በንግግር የመፍታት ልምድን ማዳበር እንደሚገባም ከንቲባው አክለዋል።
ከተማዋ በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እና የመሠረተ ልማት እጦት ውስጥ መውደቋን የገለጹት ከንቲባው አኹን ላይ ያለውን አንጻራዊ ሰላም ተጠቅሞ የነዋሪዎቹን የመልማት መብት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ የአካባቢው ተወላጆች ከመሪዎች ጋር ተቀናጅተው ሊሠሩ እንደሚገባም ነው የገለጹት።
በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍል ተወካዩች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!