የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት!

60

በጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ሥራ ኢትዮጽያን የሚመጥን እና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት የጣለ ነው።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ”ጸሐይ 2” የተሰኘች እና በአየር ኃይሉ የተሠራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ አድርጓል።

አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት። ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመኾን የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

Previous articleየደቡብ ጎንደር ዞን ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወደ ዞን ማዕከል ገቡ፡፡
Next article“ገዥ ትርክትን በማስረጽ፣ በትጋት እና በቁርጠኝነት ይሠራል” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)