
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ እና የእብናት ወረዳ ምልምል ወጣቶች መከላከያን እና የክልሉን የጸጥታ ተቋማት ለመቀላቀል ወደ ማሠልጠኛ ማዕከል መሸኘታቸው እና ወደ ዞን ማዕከል መድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡
ምልምል ወጣቶቹ በየወረዳቸው አሸኛኘት እንደተደረገላቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሀገራቸውን ከውጭ እና ከውስጥ ጥቃቶች ለመከላከል ብሎም የሀገራቸውን ልማት ለማስቀጠል በማሰብ የመከላከያ ሠራዊትን እና የክልሉን የጸጥታ ተቋማት ለመቀላቀል ምልምል ወጣቶቹ ወደ ዞን ማዕከል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
መከላከያን እና የክልሉን የጸጥታ ተቋማት መቀላቀል የሀገራቸውን ሕዝብ መጠበቅ እና ልማትን ማፋጠን እንደኾነ በመገንዘብ ተቋሞቹን ለመቀላቀል መወሰናቸውን አስረድተዋል፡፡
ምልምል ወጣቶቹ ሌሎችም ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን እና የክልሉን የጸጥታ ተቋማት በመቀላቀል ሀገራቸውን እና ክልላቸውን እንዲጠብቁም ነው ያሳሰቡት፡፡
ምልምል ወጣቶቹ ወደ ዞን ማዕከል ሲደርሱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!