
ደሴ: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ከወጣቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማዋ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍ ተመሳሳይ የሰላም ውይይቶች ከመንግሥት ሠራተኞች ፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከፀጥታ አካላት እና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር መካሄዱን ተናግረዋል።
ወጣቶች የሚያነሱትን የሥራ አጥነት ችግር ከተማ አሥተዳደሩ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራበት የተናገሩት አቶ መሐመድ አሚን አሁን በከተማዋ እና አካባቢው ያለውን ሰላም ወጣቱ እንዲያፀና ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ሰልሃዲን ሰይድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!