
ደብረ ብርሃን: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ ተከብሯል።
በዓሉን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ እና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቅምብቢት ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በጋራ አክብረውታል።
የበዓሉ ታዳሚዎች ይህንን በዓል ስናከብር ለዘመናት ይዘነው የዘለቅነውን አብሮነት ለማስቀጠል ይረዳናል ብለዋል።
“እኛ ለመለያየት የምንከብድ የጤፍ ዘር ነን” ሲሉ ቁርኝታቸውን የገለጹት ተሳታፊዎቹ ይህንን አንድነታችንን ለበጎ ተግባር እንጠቀምበታለን ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኀላፊ ሜሮን አበበ መልካም እሴቶቻችንን ለመለዋወጥ እና አንድነታችንን ለማጠንከር ባለመ መልኩ በዓሉን በጋራ አክብረናል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!