
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ክልላዊ የፓርቲው የምሥረታ በዓል “የሃሳብ ልዕልና፤ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት እና የፓርቲው የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ፓርቲው ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲፈጠር፣ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ፣ አብሮነት እና አንድነት እንዲያድግ አድርጓል ነው የተባለው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!