
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በስላሴ ጉልት ገበያ ያስገነባውን የገበያ ሸድ ለ526 ነጋዴዎች አስረክቧል።
የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር አገልግሎት ጽሕፈት ቤት አሥተባባሪነት በማኅበረሰቡ ተሳትፎ እና በረጅ ድርጅቶች ድጋፍ የተገነቡ የገበያ ሸዶች ለተጠቃሚው መተላለፋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የከተማዋን ሰላም ከማስከበር ጎን ለጎን የልማት እና መልካም አሥተዳደር ግንባታ ሥራንም ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደኾነ ነው የተገለጸው፡፡
በስላሴ ገበያ ማዕከል ይሠሩ የነበሩ 108 ሴት ነጋዴዎች በተሠራው የልማት ሥራ ተጠቃሚ መኾናቸውን ከከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!