
ደብረ ማርቆስ: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ወጣቶቹ የአካባቢያቸውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በክፍለ ከተሞች ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሰላሙ መደፍረስ በወጣቶች ላይ የሥነ ልቦና ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳደሯል፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ ወጣቶች የእለት ተዕለት ሕይወታቸውን ለመምራት የሰላሙ መደፍረስ ፈታኝ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ወጣቶቹ በየከፍለ ከተሞቻቸው በሰላም ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲኾን የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ተጋግዘን እንሠራለን ብለዋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ አበባው ግዛቸው በከተማ አሥተዳደሩ እና በክፍለ ከተሞች የሚደረጉ የሰላም ውይይቶች ፍሬያማ ናቸው ብለዋል፡፡
ወጣቶች ተምረው ሀገር የሚረከቡት ሰላም ሲፈጠር በመኾኑ ለሰላም መትጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማን ሰላም በዘላቂነት በማጽናት በከተማዋ የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ኀላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!