“የኮሪደር ልማቱ የባሕርዳርን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው” መለስ ዓለሙ

35

ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ባሕር ዳር የገቡት ከፍተኛ መሪዎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መለሰ ዓለሙ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

መሪዎቹ በጣና ሐይቅ ዳርቻ እየተገነባ የሚገኘውን የጣና ማሪና እና በከተማ እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማቶችን ነው የተመለከቱት።

በሚኒስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መለስ ዓለሙ ብልጽግና ፓርቲ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል። በባሕርዳር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን መመልከታቸውን ነው የተናገሩት። በባሕርዳር ከተማ እየተገነቡ ያሉ የልማት ሥራዎች የኮሪደር ልማት እሳቤ እየሰፋ መምጣቱን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

ከግቢ የጀመረው የገበታ ፕሮጄክት ወደ ሀገር መስፋቱን አእና በርካታ ፕሮጄክቶችን መፈጸሙን የተናገሩት ኀላፊው የኮሪደር ልማትም ከአዲስ አበባ ጀምሮ ወደ ሀገሪቱ ታላላቅ ከተሞች መስፋቱን ተናግረዋል።

በባሕርዳር የተመለከቱት የኮሪደር ልማት ተስፋ ሰጪ እና ጥሩ ጅማሮ መኾኑንም ገልጸዋል። ባሕርዳር ከተማ በተፈጥሮዋ ውብ ከተማ ናት ያሉት ኀላፊው የኮሪደር ልማቱ ውበቷን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል። ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ ምቹ ፣ ክልሉን እና ኢትዮጵያን የምትመጥን ከተማ እንድትኾን ያደርጋታል ነው ያሉት።

የቱሪዝም ከተማ በመኾኗ የኮሪደር ልማቱ የቱሪዝም እንቅስቀሴዋን የበለጠ ያሳድገዋል ብለዋል። የኮሪደር ልማቱ አዲስ የሥራ መንፈስ የሚያላብስ እና የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። አጀማመሩ ትልቅ እና ውብ መኾኑን ነው የገለጹት።

የሕዝቡን የልማት ፍላጎት የሚያጎለብት እና የኢትዮጵያ ብልጽግና የማይቀር መኾኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል። ባዩት ነገር መደሰታቸውንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባቡር መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ዝርፊያ የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታዎቀ፡፡
Next article“የክልሉ እና የሀገር ብልጽግና እንዲረጋገጥ እየተሠራ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)