
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ባሕርዳር የገቡት የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ መሪዎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር)፣ በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
መሪዎቹ በጣና ሐይቅ ዳር እየተገነባ የሚገኘውን የጣና ማሪና ፕሮጄክትን ነው እየጎበኙ የሚገኙት። የጣና ማሪና ፕሮጀክት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን በማላበስ የቱሪዝም እንቅስቃሴን እንደሚጨምር ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!