ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር እየሠራ መኾኑን የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

81

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የነዳጅ ጥቁር ገበያን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ፈንታሁን ፈጠነ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አሽከርካሪዎቻቸው የቀዱትን ነዳጅ በአግባቡ መጠቀማቸውን የመቆጣጠር ቸልተኝነት አለ ብለዋል።

ነዳጅን በሕገ ወጥ መንገድ እንዲወጣ በማድረግ ተሳትፎ አላቸው ባላቸው አካላት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ መኾኑንም አንስቷል።

ምክትል ኀላፊው 135 ሺህ 507 ሊትር ወይም (ሦስት ቦቴ እስከ ተሳቢው) በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዟልም ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በባሕር ዳር የሚሠራው የኮሪደር ልማት የከተማዋን የተፈጥሮ ውበት ይበልጥ እየገለጠ ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተሥፋዬ
Next articleወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ይደረግ።