
አዲስ አበባ: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የ5ኛው ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲኔት አፈፃፀም ግምገማ አጋር እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ድኤታ መለሰ መኮንን መንግሥት ትርጉም ባለው ዘላቂ ልማታዊ ሴፊቲኔት የዜጎችን ሕይዎት ለማሻሻል እና ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ መኾኑን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ዓመታት የዜጎች ሕይዎት ላይ ለውጥ ያመጡ ውጤታማ ሥራዎች ተመዝግበዋል ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታ ሳማሪታ ሰዋሰው በ2017 በጀት ዓመት ከዓለም ባንክ የልማት ፖሊሲ ትግበራ ጋር በተያያዘ 45 ቢሊዮን ብር ለገጠር ሴፊቲኔት ፕሮግራም ጥቅም ላይ መዋሉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም 9 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎችን በገጠር እና በከተማ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትር ድኤታ ሳማሪታ ተናግረዋል።
የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሠራው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የጠቆሙት።
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!