የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማትን የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።

34

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ የባሕር ዳር ከተማን የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

በምልከታቸው ላይ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተሥፋዬ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢዎች እና አባላት ተገኝተዋል።

የምክር ቤት ዓባላቱ በከተማዋ የሚካሄደውን ልማት ከተመለከቱ በኋላ በግንባታው ላይ የሚሳተፉ ሠራተኞችን ምሳ በመጋበዝ ያበረታታሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተፈጠረው ቀውስ ወደ ሰላም ይመጣ ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
Next articleጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ማስፋት እንደምትፈልግ አስታዎቀች።