
እንጅባራ: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፍቅሬ በፈቃዱ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ መከበር የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላቸውን እና ወጋቸውን ለሌሎች እንዲያስተዋውቁ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ውብ ባሕሎች ባለቤት ናት ያሉት አፈ ጉባኤዋ ባሕሎችን በማልማት እና በመጠበቅ ለሀገር እድገት የሚኖራቸውን አበርክቶ ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ወንድማማችነትን ማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት መጎልበት ፋይዳው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።
ላለፉት 18 ዓመታት የተከበሩ በዓላትም የተለያዩ ብሔር እና ብሔረሰቦችን በማቀራረብ እና ባሕልን ከባሕል ጋር በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!