በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ወንድማማችነትን ማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት መጎልበት ፋይዳው የጎላ ነው።

38

እንጅባራ: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፍቅሬ በፈቃዱ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ መከበር የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላቸውን እና ወጋቸውን ለሌሎች እንዲያስተዋውቁ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የበርካታ ውብ ባሕሎች ባለቤት ናት ያሉት አፈ ጉባኤዋ ባሕሎቻችን በማስተዋወቅ እና በመጠበቅ ለሀገር እድገት የሚኖራቸውን አበርክቶ ማሳደግ ይገባል ብለዋል። የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል
ወንድማማችነትን ማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት መጎልበት ፋይዳው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።

ላለፉት 18 ዓመታት የተከበሩ በዓላትም የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን በማቀራረብ እና ባሕልን ከባሕል ጋር በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመልማት ጥያቄዎች የሚመለሱት በራስ አቅም ከሚሠበሠብ ገቢ ነው።
Next articleየብሔር ብሔረሰቦች ቀን ባሕል እና ወግን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና አለው።