ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በውጤታማ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

29

ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በውጤታማ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው አህጉር አቀፍ ጉባዔ “የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ከጉባዔው ጎን ለጎን ከሩዋንዳ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ (ዶ.ር) ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ልምድን እና እውቀትን በመጠቀም ለሰላም ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል መኾኑን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰላሙ ኹኔታ መሻሻል በማሳየቱ የግብር አሠባሠቡ ተነቃቅቷል።
Next articleግብርን እንደ ዕዳ መቁጠር ለገቢ አሠባሠብ እንቅፋት ኾኗል።