ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

29

አዲስ አበባ: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ዛሬ እየተከናወነ ነው። መድረኩን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመኾን ያዘጋጁት ነው።

የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት በዓለም ለ16ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ10 ጊዜ “ኢንተርፕርነርሺፕ ለሁሉም” በሚል መሪ መልዕክት ከኅዳር 9/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲከበር ቆይቷል።

በሳምንቱ የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲኾን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት እና የዙም ኮንፈረንስ፣ በሥራ ፈጣሪዎች መካከል የልምድ ልውውጥ የተደረገበት የእሳት ዳር ጨዋታ እንዲሁም ሥራ ፈጣሪዎች ይዘዋቸው የመጡትን የሥራ ዕድሎችን አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ጀማሪ እና ነባር ሥራ ፈጣሪዎች በተገኙበት በኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ነው እየተከናወነ የሚገኘው።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ።
Next articleምክር ቤቱ አቶ ሐጂ ኢብሳን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ምክትል ዋና ኦዲተር አድርጎ ሾመ፡፡