
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ እያካሄደው ባለው 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን ተጨማሪ ረቂቅ በጀት መርምሮ አጽድቋል።
ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ.ር) በጀቱ የሚውልባቸውን ዋና ዋና ዘርፎች ዘርዝረዋል።
ይህም ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊዮን ብር እና ለወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ 119 ቢሊዮን ብር መኾኑን ገልጸዋል።
ይህን በዝርዝር ሲያስረዱም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ 185 ቢሊዮን ብር፣ ለማኅበራዊ ድጎማ 208 ቢሊዮን ብር፣ ለማኅበራዊ ሴፍቲኔት ማስፋፊያ 60 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ 10 ቢሊዮን ብር እና የወጪ አሸፍፈን ማስተካከያ ለማድረግ 119 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ተወያየቶ በሦስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ተጨማሪ በጀቱን አጽድቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!