ፌዴራል ፖሊስ በአፍሪካ ጠንካራ የፖሊስ ተቋም ለመኾን እየሠራ ነው።

61

አዲስ አበባ: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም ኮንፈረንስ ታሳታፊ እንግዶች የፌዴራል ፖሊስ ተቋማትን እየጎበኙ ነው። በጉብኝቱ ወቅት ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ የኢትዮጵያ የሕግ ማስከበር ልምድ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ ነው ብለዋል። ዘመናዊ ፖሊስ በኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ስለመኾኑ አብራርተዋል።

ፌዴራል ፖሊስ በአኹኑ ጊዜ ጥፋቶችን የማስቆም፣ ከተፈፀሙ በኋላም ምላሽ የመስጠት ብቻ ሳይኾን ቅድሚያ ወንጀልን የመከላከል መርህን የሚከተል ነው። ፌዴራል ፖሊስ በአኹኑ ጊዜ ሙያዊ እና ጠንካራ በኾነ መልኩ ለውጥ ተደርጎለት እየሠራ ያለ ተቋም መኾኑን አብራርተዋል። በአኹኑ ጊዜም በአፍሪካ ጠንካራ የፖሊስ ተቋም ለመኾን እየሠራ ያለ ስለመኾኑ ነው ያብራሩት።

በሰው ኀይል፣ በሥልጠና፣ በሙያ፣ በትጥቅ፣ በተሽከርካሪ እና መሰል ዘመናዊ አደረጃጀት ያለው ጠንካራ የሀገሪቱ የጸጥታ ኀይል መኾኑንም አስገንዝበዋል። ፖሊስ በአኹኑ ጊዜ ድንበር ዘለል ሕገወጥነትን በመከላከል አንደ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገወጥ የመሣሪያ እና ሕገወጥ የመድኃኒት ዝውውር ለመከላከል ተልዕኮን በአግባቡ የሚፈጽም ተቋም ነው ብለዋል።

ፌዴራል ፖሊስ አኹን ላይ ከዓለም አቀፉ ፖሊስ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የፖሊስ ተቋማት ጋር በጋራ የሚሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰላም እጦት የፈተነው ጥምር ግብርና
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ።