
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳዎች እና በደብረ ወርቅ ከተማ አሥተዳደር ስር በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ሕዝባዊ የሰላም ውይይቶች መካሄዳቸውን የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ቶራሜዳ ቀበሌ ነዋሪዎች ባካሄዱት የሰላም ውይይት በወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ፣ በቀጣይ የልማት፣ የትምህርት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በሌሎች ተግባራት ዙሪያ መክረዋል።
በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ 08 (የዶማ ) ቀበሌ ነዋሪዎችም የሰላም ውይይት አካሂደዋል።
በተመሳሳይ በደብረወርቅ ከተማ አሥተዳደር የደጅ አጋምና የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የሰላም ዉይይት አካሂደዋል።
ነዋሪዎቹ በሰላምና ጸጥታ፣ በልማትና በትምህርት ሥራዎች ዙሪያ ዉይይት አካሄደዋል።
በዉይይቱ የአካባቢያቸውን ሰላም ከአካባቢው አሥተዳደር ጋር በመቀናጀት እንደሚያስጠብቁ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን ደህንነት እንደሚያስጠብቁና መደበኛ ሥራቸዉን እንደጀመሩ ገልጸዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ከመንግሥት ጎን ሆነው በመሥራታቸው የሰላም ሁኔታው እየተሻሻለ እንደሚገኝ የዞኑ አሥተዳደር ማስታወቁ ይታወሳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!