
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ከመኸር ሰብል መሰብሰብ ጎን ለጎን ትኩረታቸውን በበጋ መስኖ ልማት ላይ አድርገዋል።
ለመስኖ ልማት የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ፦
🌱 በያዝነው ዓመት 1 ሚሊዮን 197 ሺህ 28 አርሶ አደሮች በመስኖ ልማት ይሳተፋሉ።
🌱 60 በመቶ የሚጠጉ አርሶ አደሮች መስኖ ማልማት ጀምረዋል።
🌱 487 የአርሶ አደሮች የመስኖ ልማት ውይይቶች ተካሂደዋ።
🌱 በውይይቶቹ 248359 አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡
🌱 6 ሺህ 237 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመስኖ ቦይ ጠረጋ ተካሂዷል።
– በዘመናዊ የተጠረገ የመስኖ ቦይ 1397 ኪሎ ሜትር
– በባሕላዊ የተጠረገ የመስኖ ቦይ 4840 ኪሎ ሜትር
🌱 በመስኖ ሰብል አመራረት የጊዜ ሰሌዳ ለ94 ሺህ 885 አርሶ አደሮች እንዲዘጋጅላቸው ተደርጓል።
🌱 የዘንድሮውን መስኖ በሜካናይዜሽን ለማገዝ እየተሠራ ነው።
ምንጭ፦ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!