
በሱፍቃድ ሪል እስቴት በአረርቲ ከተማ በ5 ቢሊዮን ብር አንድ ሺህ የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ይገኛል። በ23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አንድ ሺህ የመኖሪያ ቤትን በ5 ቢሊዮን ብር እየገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን ለቀጣይ ሁለት አመት የኩባንያውን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
ከተመሰረተ ገና የሁለት ዓመታት ዕድሜ ያለውና በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቤት ፈላጊዎችን ምርጫ ያሟላ ዘመናዊ መንደር እየገነባ ይገኛል። ከዋና ከተሞች ወጣ ብሎ ወረዳዎችንና አዳጊ ከተሞችን በማነቃቃት፣ የኢንዱስትሪ ልማት ፍሰትን የሚያግዝ፣ የማኅበረሰቡን አኗኗር በማዘመን የከተማ ልማት እያፋጠኑ ከሚገኙ ጥቂት ፕሮጀክቶች ቀዳሚ ነው።
በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የመኖሪያ መንደር ለቤት ደንበኞቹ አስተማማኝ የቤት ግንባታ አገልግሎት እና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ አሳታፊ የከተማ ልማት ፍልስፍና ይከተላል። የበሱፍቃድ ሪል እስቴት ልማት ኩባንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንጃር ሸንኮራዋ አረርቲ ከተማ ስትጠራ ስሙ አብሮ የሚነሳው በሱፍቃድ ሪል ስቴት በ230 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ እየተገነባ ያለው ግዙፍ የመኖሪያ መንደር 1ሺህ ቤቶችን፣ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል፣ ከአጸደ-ሕጻናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም እና የጤና ተቋማት፣ ለስምጥ ሸለቆዋ የቱሪስት መዳረዋ አረርቲ ተስማሚ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ አዲስ መንደር ነው።
በሱፍቃድ ሪል እስቴት በአጭር ጊዜ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የቤት ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን፣ ከሰሜን አሜሪካና ካናዳ፣ እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ እና ቻይና ሀገራት የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ በስፋት የቤት ደነበኞቹ የሚገኙባቸው ሀገራት ናቸው። ይህ ዓለም-አቀፍ ተደራሽነቱን እያሰፋ በመሄድ ሌሎች ሀገራትንም የመድረስ ስትራቴጂ ነድፎ እየሠራ ሲሆን የብራንድ አምባሳደሯ ሹመትም የዚሁ አካል ነው።
አዳጊ የሆነችውን አረርቲ ከተማ ከአዳማ፣ ደብረዘይት፣ ሞጆ፣ ደብረብርሃን እና አዲስ አበባ ጋር በልማት፣ የቱሪስት መዳረሻ እና በኮንፈረንስ ቱሪዝም የማስተሳሰር አቅም እየፈጠረ የሚገኘው የቤት ልማት ኢንቨስትመንት ብራንዱን ይበልጥ ለማሳደግና በቀጣይም ዓለም-አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ነው ፡፡
በሱፍቃድ ሪል እስቴት ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ዓመታት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን ሾሟል።