
ባሕር ዳር: ኅዳር 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተች መኾኑን በአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ ተናገሩ።
የአፍሪካ አሕጉራዊ የሰላም ኮንፈረንስ “የበለፀገች እና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ በዚሁ ወቀት እንደተናገሩት በአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ማስፈን ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የቀጣናውን ብሎም የአሕጉሪቷን ሰላም ለማረጋገጥ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተች መኾኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ካሳየው ቁርጠኝነት ባሻገር በሽግግር ፍትህ አማካኝነት ዘላቂ ፍትህ እና ሰላምን ለማረጋገጥ አብነት የሚኾን ሥራ እያከናወነ መኾኑን ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!