ጦርነት ሰልችቶናል ሰላም እንፈልጋለን!

241

ባሕር ዳር: ኅዳር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንቦሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በዛሬው እለት “ጦርነት ሰልችቶናል ሰላም እንፈልጋለን” ብለው በነቂስ ወጥተው ድጋፋቸውን በዚህ መልኩ ገልፀዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ሰላም ለሰው ልጆች አስፈላጊ ነው፣ ደም መፋሰስና መገዳደል ይብቃ፣ ሰላም የሚሰፍነው በጋራ መሥራት ስንችል ነው የሚሉና ትምህርት እና ልማት እንዲቀጥል የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።
ነዋሪዎቹ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ካስተላለፏቸው መፈክሮች መካከል ፡-
👉 እኛ አርሶ አደሮች ሰላምና ልማት ፈላጊዎች እንጂ ጦርነት ናፋቂዎች አይደለንም!!!
👉 ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ ውድ በረከት ሲሆን የሚረጋገጠውም በሁላችን ትብብር ነው!!!
👉 የራስን ወንድም በመግደል የአማራ ህዝብ ጥያቄ አይፈታም!!!
👉 መከላከያ ሠራዊትን አለማክበር የሚሞትለትን ሀገር እንደመድፈር ይቆጠራል!!!
👉 ህፃናት ልጆቻችን ከታወጀባቸው ድንቁርና ወጥተው የመማር መብታቸው ይከበር!!
👉 ልማቱም ሆነ እድገቱ እውን መሆን የሚችለው ሰላም ሲሰፍን ብቻ ነው!!
👉 የጠነከረ ወንድማማችነትን መገንባት የፈተናዎች ሁሉ መሸጋገሪያ ድልድይ ነው!!!
👉 ሰላም ስንኖረው ቀላል ስናጣው ደግሞ ከባድ ነውና ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን!!!
👉 ደም መፋሰስ መገዳደል ይብቃ!!!
👉 ፍላጎታችን ሰርተን ሀገር መገንባት እንጂ ሀገር ማፍረስ አይደለም!!!
👉 ሰላም የሚሰፍነው በጋራ መሥራት ስንችል ነው የሚሉና ሌሎች የሰላም ጥሪን የያዙ መፈክሮችን በማሰማት የድጋፍ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ከወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ጎንደር ዞን የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።
Next articleእይታችን ብቻ ሳይኾን ሠርቶ የመለወጥ ተስፋችንም ተመልሷል።