
ባሕር ዳር: ኅዳር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ጎንደር ዞን የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።
ዞኑ በተለይም በሩዝ ምርት የሚታወቅ እና ትርፍ አምራች አካባቢ ነው። ከፍተኛ መሪዎች ከደራ ወረዳ ጀምሮ የልማት ሥራዎች ምልከታ አድርገዋል። ጉዟቸውን በመቀጠልም በፎገራ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች የሚለማውን ሰብል እና ሌሎችንም የልማት ሥራዎች እየተመለከቱ ነው። የየአካባቢው ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮችም ለከፍተኛ መሪዎቹ አቀባበል አድርገዋል። መሪዎች በፎገራ ወረዳ በተዘጋጀው የገበሬዎች በዓል ላይም ይሳተፋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!