የደብረ ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት የጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱ ከሪም መንግሥቱ ጎበኙ።

42

ደብረ ብርሃን: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢዋ ያለውን የጤና አገልግሎት ለማስፋት በ2009 ዓ.ም ነበር የደብረ ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል ግንባታው የተጀመረው።

በወቅቱ በ251 ሚሊዮን ብር ግንባታው ቢጀመርም በመካከል በገንዘብ እጥረት ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ በቀለ ገብሬ ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም በ700 ቀናት ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ መንቆረር ከተባለ የግንባታ ተቋራጭ ጋር አዲስ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራ መገባቱንም ኀላፊው አስረድተዋል፡፡

የግንባታ ሂደቱም አሁን ላይ 63 በመቶ መድረሱ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ የባከነውን ጊዜ በማካካስም በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሠራ ስለመኾኑም ነው የተብራራው፡፡

በ1 ቢሊዮን ብር በሚጠጋ በጀት እየተገነባ ያለው የደብረ ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል 300 የታካሚ አልጋዎች የሚኖሩት ሲኾን ከከተማዋም አልፎ ለአጎራባች አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተስፋ ተጥሎበታል።

ዘጋቢ፡- ለዓለም ለይኩን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበትምህርት ተቋማት በሚገኘው ዕውቀት ሀገራዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚገባ አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) አሳሰቡ።
Next articleየዳኝነት እና የፍትሕ ተቋማት የትብብር መድረክ መቋቋሙ የፍትሕ ሂደቱን ቀልጣፋ እና ተደራሽ እንደሚያደርገው ተጠቆመ።