
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ እና በወረታ ከተማ አሥተዳደር በተለያዩ ቀበሌዎች የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የምህረት እና የይቅርታ ጥሪ በመቀበል በይቅርታ መግባታቸው ይታወቃል።
የፎገራ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያመለክተው በይቅርታ የገቡ አካላት ከዞን ከፍተኛ መሪዎች ፣ ከዞን ደጋፊ መሪዎች እና ከሁለቱም ወረዳ አሥተዳደር መሪዎች ጋር በቀጣይ ከሕግ ማስከበር እና ከሰላም ግንባታ አንፃር በጋራ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!