ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ አልሞ እየሠራ መኾኑን የባሌ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

17

አዲስ አበባ: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምርት ዘመኑ ከ580 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈኑን የበኦሮሚያ ክልል የባሌ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አልዩ ሙሐመድ ገልጸዋል።

ከዚህም ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል። አርሶ አደሮችን በማደራጀት ስንዴ በኩታ ገጠም በስፋት እየለማ ነው ያሉት ኀላፊው በበጀት ዓመቱ ከ14 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።

ስንዴ በአማካኝ በሄክታር ከ41 እሰከ 60 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይታሰባል ነው ያሉት። በባለፈው ዓመት የሰንዴ በሽታ ተከስቶ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከግብርና ምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ለውጥ ማምጣት እንደተቻለም ገልጸዋል።

በዞኑ ከ280 በላይ ትራክተር እና ከ60 በላይ የምርት መሰብሰቢያ ኮንባይነር በሥራ ላይ መኾናቸውንም ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ፦ ቴወድሮስ ደሴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰልጣኞች በተመረቁበት የሙያ መስክ ለክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
Next articleየደብረ ብርሃን ጤና ጣቢያ ያስገነባውን ህንጻ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ፡፡