ኢንስቲትዩቱ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።

70

ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎች መካከል በኢንስቲትዩቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ይገኝበታል።

የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና በሥስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 222 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው። ከተመራቂዎቹ መካከል 58ቱ ሴቶች ሲኾኑ አንድ ተመራቂ ደግሞ የሦስተኛ ዲግሪ ሰልጣኝ ነው።

ተመራቂዎቹ በፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በፐብሊክ ፖሊሲ እና አመራር እንዲሁም በፖለቲካል ኢኮኖሚ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕገ ወጥ ንግድ እና ነጋዴዎች የኑሮ ውድነቱን እያባባሱት ነው” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች
Next article“ብልጽግና ዕውነተኛ ኅብረ ብሔራዊነትን እና አንድነትን በሚዛኑ አስተሳስሮ ተጫባጭ ለውጥ አምጥቷል” አቶ አደም ፋራህ