“የኢትዮዽያ ኪነ-ህንፃ፣ ኪነ-ውበትና ኪነ-ጥበብ አድባር የሆነችው ጎንደር ሥራ ላይ ነች” አሕመዲን መሀመድ

68

ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሀመድ (ዶ.ር) በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት ዕድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በምሽት ተዘዋውረን ተመልክተናል ብለዋል።

በሥራ ላይ ያሉትን የከተማው አመራሮች፣ ኮንትራክተሮችና ብርቱ የሆኑትን ወጣት ሠራተኞችም ማበረታታቸውንም ገልጸዋል።

ጎንደር ሰላሟ ተመልሶ የልማት ፕሮጀክቶቿ ቀን ከሌሊት በቀን 22 ሰዓታት ሥራ በመሥራት እየተፋጠኑ እንደሚገኙም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አመላክተዋል።

ጉብኝቱ የከተሞች ከንቲባዎችና ሥራ አስኪያጆች ልምድ የተለዋወጡበት እና የሥራ ባህላችንን ከማዳበር አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መኾኑን ተረድተናል ብለዋል።

በከተሞቻችን እየተከናወኑ ያሉት የልማት ሥራዎች በጥራትና በፍጥነት እንዲከናወኑ አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleንደ ዓድዋ ያሉ የጋራ ታሪኮችን በማጉላት የኢትዮጵያውያንን ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት !