ንደ ዓድዋ ያሉ የጋራ ታሪኮችን በማጉላት የኢትዮጵያውያንን ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

23

ወልድያ: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በወልድያ ከተማ “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በፓናል ውይይት ተከብሯል። የከተማ አሥተዳደሩ አፈ ጉባኤ ዓለማየሁ ነጋ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲከበር እየገጠሙት ያሉትን ተግዳሮቶቹን ለመሻገር የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ማስቀመጥ እንደሚገባ ነው ተናግረዋል፡፡ ኅብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የበለጠ የሚጎለብትበትን አቅጣጫ መከተል እንደሚገባም አሳስበዋል።

በወልድያ ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ ገብሬ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማረም እና የጋራ ታሪክን በማጎልበት የኢትዮጵያውያንን አብሮነት ማጎልበት ይገባል ብለዋል። እንደ ዓድዋ ያሉ የጋራ ታሪኮችን በማጉላት የኢትዮጵያውያንን ትስስር ማጠናከር ይገባልም ነው ያሉት።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የአማራ ክልል ተወካይ እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኀላፊ አስናቀች ኃይሌ ኢትዮጵያ የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ሀገር በመኾኗ እርስ በእርስ መከባበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ29 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየሠራ መኾኑን በኦሮሚያ ክልል የአርሲ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
Next article“የኢትዮዽያ ኪነ-ህንፃ፣ ኪነ-ውበትና ኪነ-ጥበብ አድባር የሆነችው ጎንደር ሥራ ላይ ነች” አሕመዲን መሀመድ