በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሕዝብ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመለየት ለመፍታት እየተሠራ ነው።

59

ከሚሴ: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ መልእክት የእግር ጉዞ እና የፓናል ውይይት ተካሄዷል። በእግር ጉዞው እና በፓናል ውይይቱ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች እና የብሔረሰብ አሥተዳደሩ መሪዎች ተሳትፈዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመለየት ለመፍታት እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ኀብረብሔራዊነቷ የተረጋገጠ እና የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ተራማጅ አስተሳሰብና ሰው ተኮር የሆነ ሥራ እያከናወነ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ሁሌም ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፤ ታጥቀው በየአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አካላትም ችግሮችን በመሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሰከነ ውይይትን ሊመርጡ ይገባል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኀላፊ አሕመድ ሁሴን ባለፉት አምስት ዓመታት እንደሀገር የገጠሙንን በርካታ ችግሮች እንደ መስፈንጠሪያ እድል በመጠቀም በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊውያን የተሳተፉበት ሀገረ መንግሥት በመገንባት ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ ሀገር እውን ለማድረግ ፓርቲው ከሕዝብ ጋር እየተሠራ ነውም ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊውያን የተሳተፉበት የጋራ ትርክት በመፍጠር በጋራ ለመልማት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል ኀላፊው።

የውይይቱ ተሳታፊ የብልፅግና ፓርቲ አባላት በበኩላቸው አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ሲከበር የተያዘው የቁጭት እቅድ እንዲሳካ ርብርብ በማድረግ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleራስን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል የአካባቢያቸውን ንጽህና እንደሚጠብቁ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next articleከ29 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየሠራ መኾኑን በኦሮሚያ ክልል የአርሲ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።