“የተደረገልን አቀባበል የቤታችን ያህል እንዲሰማን ያደረገ ነው” አዲስ ገቢ ተማሪዎች

50

ጎንደር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመማር ማስተማር ሂደቱ ያግዙኛል ያላቸዉን ተግባራት አከናውኗል። ተማሪዎችን ህዳር 12 እና 13/2017 ዓ.ም እየተቀበለ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርስቲዉ ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የጤና፣ የስፖርት፣ መዝናኛ፣ የምግብ፣ የዶርም እና ለመማር ማስተማር ሒደቱ የሚያግዙ ቁሳቁሶች መሟላታቸዉን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ሃይማኖት በላይ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ እንደ ባለፉት ዓመታት ሁሉ የትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ የመደበለትን የ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያመጡ 1 ሺህ 24 ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ሲከታተሉ ቆይተዉ ዉጤት የመጣላቸዉን ጨምሮ 2 ሺህ 831 ተማሪዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ፈተና ወስደዉ ዉጤት ያልመጣላቸዉ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም የሚማሩ ተማሪዎች ከጥር ወር በኋላ እንደሚቀበሉም ተናግረዋል፡፡

ለአሚኮ አስተያየታቸዉን ከሰጡን ተማሪዎች መካከል ተማሪ በላይነሽ አዳነ እና ተማሪ አብዩ ገብሬ “ጎንደር እና አካባቢዉ ሰላሙ የተረጋጋ” መኾኑን ስለመታዘባቸዉ ነግረውናል፡፡

በዩኒቨርስቲዉ አሥተዳደር እና በተማሪዎች እየተደረገላቸዉ የሚገኘዉ አቀባበል የቤታቸዉ ያህል እንዲሰማቸዉ እንዳደረገም ገልጸዋል።

ዘጋቢ: ደስታ ካሣ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት እንደሚያስችል ተገለጸ።
Next articleራስን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል የአካባቢያቸውን ንጽህና እንደሚጠብቁ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡