
ጎንደር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ እስከ 12:00 ሰዓት የነበረው የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ እገዳ ለተመረጡ 118 ባጃጆች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ተፈቅዷል።
የከተማ አሥተዳደሩ ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ሞላ ደርሶ እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድርስ አገልግሎት የሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በሥነ ምግባር የተመሠገኑ እና ከአሁን በፊት በወንጀል ያልተጠረጠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የምሽት የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር 118 ባጃጆች በተለያዩ መመልመያ መስፈርቶች በከተማዋ ከሚገኙ 11 የባጃጅ ማኅበራት የተመረጡ መኾናቸውን አስረድተዋል።
አገልገሎቱን እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ባጃጆች የመለያ ስቲከር በመለጠፍ፣ ለባለንብረቶች የምሽት የሥራ መርሐ ግብር፣ የሥራ ውል እና የምሽት አገልግሎት መስጫ ባጅ በመስጠት አገልግሎቱን ማስጀመራቸውን ገልጸዋል። ከኅዳር 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ የገቡ ሲኾን በቀጣይ ቁጥሩን ለመጨመር ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
አገልግሎት የሚጠቀሙ አካላት የምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ባጃጆች መለያ ያላቸው መኾኑንም ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
