ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ነጻነትን እና የአፍሪካን ሰላም ለመጠበቅ ያደረገችውን አስተዋጽኦ የሚያስተዋውቅ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂድ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

46

አዲስ አበባ: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሕጉራዊ የሰላም፣ የብልጽግና እና የልማት ኮንፈረንስ የፊታችን ሰኞ ኅዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሰላም ሚኒስትር ድኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ.ር) ጉባዔውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ አቅሟን ለመጠቀም እና የፖለቲካ ነፃነቷን ለማረጋገጥ የምትሠራው ሥራ የሚንጸባረቅበት ነው ብለዋል። የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የአፍሪካ አጀንዳ በ2063 የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ይጠቅማል የተባለው መድረክ 26 የአፍሪካ ሀገራት ይሳተፍበታል ተብሏል።

በዚህ አሕጉራዊ ኮንፈረንስ 400 ያክል ሰዎች የሚሳተፉ ሲኾን ከአፍሪካ በተጨማሪ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሌሎች ሀገራት ኢምባሲዎችም ይገኛሉ ተብሏል።

የአፍሪካ የሰላም እና ደህንነት ምክርቤት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ተወካዮች ይኾናሉ። ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እና ሰላም ለማፅናት እየሄደችበት ያለው ሀገራዊ የምክከር ኮሚሽን ሂደቱን በተሞክሮነት ያካፍላል ተብሏል።

ጉባኤው የሃይማኖት እና የባህል ተቋሞቻችን ሥራዎቻቸውን የሚያካፍሉበት አንደሚኾን ሚኒስትር ድኤታው ተናግረዋል። አንደ ዶክተር ከይረዲን ገላጻ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን እና የአሕጉሪቱን አንድነት እና ሰላም ለመጠበቅ ያከናወነችውን ሥራ ታሳያለች ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!
Next articleየአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመርቃል።