የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!

71

የኮሪደር ልማት የጣና ዳር ፈርጧ ባሕርዳርን ተጨማሪ ውበት የሚያላብሳት ከመሆኑም በተጨማሪ ለነዋሪዎቿ፣ ቱሪስቶች እና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች የምትመች የሚያደርግ ነው፡፡

ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ተገኝተን የመጀርያው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራን ተመልክተናል፡፡

በጥቂት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ የታሰበው የመጀመርያው ዙር የኮሪደር ልማት ቀን ከሌት በትጋት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው በተጀመረው ትጋት እና ብርታት ተጠናቆ ሳይክል መጠቀም ባሕላቸው ለሆነው የከተማይቱ ነዋሪዎች ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን አይተናል፡፡

መንግስት የከተሞች ውበት እና የተጥሮ ሀብት ተጠብቆ እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በትኩረት መሥራቱን ይቀጥላል፡፡

Previous articleየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሃብት በማሰባሰብ በገንዘብ ራሱን ለመቻል የሚያደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ።
Next articleኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ነጻነትን እና የአፍሪካን ሰላም ለመጠበቅ ያደረገችውን አስተዋጽኦ የሚያስተዋውቅ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂድ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።