
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከማኅበሩ የሥራ ኅላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
በማኅበሩ ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ የተመራው ቡድን የሰብዓዊ ድጋፍ በመስጠት ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶችን በተመለከተ ገለጻ አድርጓል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በመላ ሀገሪቱ የሚያከናውነውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሻሻል የሚያስችል ለውጥ ለማድረግ የሚያከናውነውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ማብራሪያ ማቅረቡን የማህበሩ መረጃ አመልክቷል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀው፤ በቀጣይ አገልግሎቱን ለማስፋት የሚያስችለውን ስትራተጂካዊ አመራር በመስጠት እና ሃብት በማሰባሰብ በገንዘብ ራሱን እንዲችል ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
