
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ መሳተፋቸው በዋናነት ከታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ጉዳዮች ለመመለስ ያግዛል፡፡
👉 ወጣቶች በግጭቶች እና አለመግባባቶች የበለጠ ተጎጅ በመኾናቸው፤
👉 ወጣቶች በኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ምጣኔ ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ቁጥር ያላቸው መኾኑ እና ይኽም በጉዳዩ ላይ ዋነኛ ከዋኝ እንዲኾኑ ስለሚያስችላቸው፤
👉 ወጣቶች ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው እና ስለነገው የሀገራቸው ጉዳይ ባለቤት በመኾናቸው፤
👉 ወጣቶች ለለውጥ ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ በመኾኑ አዳዲስ አስተሳሰቦችን እና አመለካከቶች በምክክር ሂደቶች ለማስተናገድ ቅርብ መሆናቸው፤
👉 በወጣቶች ጥያቄ የነገ ሀገር ስለምትፀና የሚሉት ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
