የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የኮሌራ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረ።

57

ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮሌራ መከላከያ ክትባት ከአንድ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ በአፍ ጠብታ መልክ የሚሰጥ ሲኾን ከ90 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ለመከተብ መታቀዱን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ ዘለዓለም ጌታቸው አስረድተዋል።

ክትባቱ ከኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወልድያ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሲስተር ሰላማዊት አያሌው የኮሌራ በሽታ ክረምት ላይ በወልድያ ከተማ እና በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ ጃራ ስደተኞች ጣቢያ ተከስቶ እንደነበር አውስተዋል።

በቅድመ ክትትል፣ ቁጥጥር እና በሽተኞችን በማከም በሽታውን መቆጣጠር ተችሏል።

በሽታው ከክትባት ባሻገር የግል ንጽህናን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ ሊቆጣጠረው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ክትባቱን ሲወስዱ አሚኮ ያገኛቸው ነዋሪዎች ክረምት ላይ በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ፍርሃት አድሮባቸው እንደነበር ገልጸዋል።

ክትባቱ በመምጣቱ እና ለሕዝቡ ተደራሽ በመኾኑ መደሰታቸውን ነዋሪዎቹ ነግረውናል።

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰብዓዊነትን በማስቀደም ደም መለገስ እንደሚገባ የደብረ ማርቆስ ከተማ ደም ባንክ አገልግሎት አሳሰበ።
Next articleወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ መሳተፋቸው ለምን አስፈለገ?