
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2017ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የፋሲሎ ክፍለ ከተማ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት እያንዳንዳቸው በ25 ካሬ ቦታ ላይ ያስገነባቸውን 42 መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ አቅመ ደካማ ለኾኑ ነዋሪዎች አስረክቧል።
የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት እንዲሟላ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የፋሲሎ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገረመው አባተ ተናግረዋል።
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች መሠረታዊ የቤት ችግርን ለመቅረፍ በማሰብ ለእያንዳንዳቸው 28 ካሬ በሚኾን ቦታ 42 ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎቹ እያስረከቡ መኾኑን ገልጸዋል።
ቤቶቹ በክፍለ ከተማው ከጎዳና ባልተናነሰ መኖሪያ ውስጥ ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች የተሠራ ነው። አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን በቅድሚያ ተጠቃሚ እንዳደረጉም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ቤቶቹ በማኅበረሰብ ተሳታፎ የተሠሩ መኾናቸውን የተናገሩት ሥራ አስፈፃሚው በ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር እንደተሠራም ተናግረዋል።
ይህን ሥራ በቀጣይ በተሻለ ጥራት እና በብዛት ለመሥራት እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
