ኢትዮጵያ አካታች እና ዘላቂ የዲጂታል ሽግግር ለማምጣት እየሠራች ነው።

45

አዲስ አበባ: ኅዳር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ አካታች እና ዘላቂ የዲጂታል ሽግግር ለማምጣት እየሠራች መኾኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ13ኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አሥተዳደር ፎረም ላይ ነው። ፎረሙ በመላው አፍሪካ ያሉ አጋር እና ባለድርሻ አካላት ቁልፍ በኾኑ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የኢንተርኔት አገልግሎ ተደራሽነትን እንዲያስፋፉ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ኢንተርኔት የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ትልቅ መሣሪያ መኾኑንም በመድረኩ አንስተዋል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ሀገር አቀፉን የኢንተርኔት አሥተዳደር ፎረም እንደምታካሂድም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በዲጂታል የለውጥ ሥራ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ለአህጉሪቱ እድገት የበኩሏን ለመወጣት ቁርጠኛ መኾኗንም አረጋግጠዋል።

ፎረሙ አጋር እና ባለድርሻ አካላት በኢንተርኔት አሥተዳድር ዙሪያ በሚኖራቸው ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል። በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጎንደር የኢትዮጵያን ሥልጣኔ እና ታሪክ ከፍ አድርጋ የምታሳይ ከተማ ናት” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!