አሚኮ የባሕር ዳርን ገጽታ በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

33

ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የውቢቷ ባሕር ዳርን ውበት በማስተዋወቅ በኩል ጥሩ ሥራ መሥራቱ ተገልጿል።

በአሚኮ እና ባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትብብር የሚቀርበው ሳምንታዊው የጣና ፈርጥ ዝግጅት የከተማዋን ውበት እና ገጽታ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መኾኑን አስተያዬት ሰጭዎች ገልጸዋል።

በባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛው ዙር ምርጫ 12ኛው ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊ የኾኑት አስተያዬት ሰጭ የጣና ፈርጥ የባሕር ዳርን ውበት ገልጦ እያሳየ ነው ብለዋል።

ይህም በርካታ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሰዎች ባሕር ዳርን ለመጎብኘት አነሳሰቷቸዋል። በመኾኑም ዝግጅቱ ባሕር ዳርን በማስቃኘት ረገድ አበርክቶው ክፍተኛ እንደኾነም አስረድተዋል።

ሌላዋ የምክር ቤት አባል እንዳሉት አሚኮ የባሕር ዳርን አስደናቂ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ገጸ በረከቶች በማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ እየተወጣ ነው።

በዝግጅቱ ከተማዋ ማሟላት ያለባትን ጉዳይ ነዋሪዎችን፣ ሀገር ጎብኝዎችን፣ ምሁራንን እና ባለሙያዎችን ጠይቆ የመፍትሔ ሐሳብ በማቅረብ ለከተማዋ በኩልም አሚኮ የሚመሰገን ሥራ ሠርቷል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የባሕር ዳር ገጽታን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ከአሚኮ ጋር መሥራቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የከተማ አሥተዳደሩ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ መምሪያ ምክትል ኀላፊ አጸደ ምንዋጋው ከአሚኮ ጋር በትብብር ለመሥራት አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።
Next articleየፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አርባምንጭ ከተማ ገቡ፡፡