
ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሸ ደሴ (ዶ.ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የቢሮ ኀላፊዎች፣ ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑት ሥራዎች ለከተማዋ ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል። የልማት ሥራዎቹ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ናቸው። ትምህርት ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የጌጠኛ መንገድ ግንባታዎችን ጨምሮ 67 ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄዎች ኾነው የቆዩ ናቸው። በከተማዋ እየተመረቁ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በከተማ አሥተዳደሩ፣ በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በግለሰቦች እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!