
ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛው ዙር 12ኛው ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔ የሁለተኛ ቀን ውሎውን እያካሄደ ነው።
የከተማ አሥተዳደሩ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ መምሪያ ምክትል ኀላፊ አጸደ ምንዋጋው የከተማ አስተዳደሩን የበጀት ዓመተት የበጀቱን መጠን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
በዚህም መሠረት የባሕር ዳር ከተማ የ2017 ዓመታዊ በጀት 4 ቢሊዮን 277 ሚሊዮን 937 ሺህ 674 ብር ኾኖ ጸድቋል።
ከዚህም ውስጥ 1 ቢሊዮን 418 ሚሊዮን 235 ሺህ 785 ብር የሥራ ማስኪያጂያ መኾኑን ወይዘሮ አጸደ ተናግረዋል።
2 ቢሊዮን 859 ሚሊዮን 696 ሺህ 889 ብር የካፒታል በጀት ነውም ብለዋል ምክትል ኃላፊዋ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
