የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)መልዕክት፦

79

ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ ሲኾን በስካንዲቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው።

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተደረገው በዚህ ትርጉም ባለው ኢንቨስትመንት ሁላችንም እንኳን ደስ አለን ለማለት እንፈልጋለን። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሂደት ላይ ብዙውን ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር በተግባር የተቆየባት ከተማ ናት።

ይኽ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል። ከዚህም ባሻገር ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ የማዋል ያለውንም ተነሳሽነት ያሳያል።

Previous articleሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ለማህጸን በር ካንሰር ክትባቱ ስኬት ርብርብ እያደረጉ መኾኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ ፡፡
Next articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት የ2017 የከተማዋን በጀት አጸደቀ።