
ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ከ40 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ልጃ ገረዶች የማሕጸን በር ካንሰር ክትባት ለመስጠት አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን የዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል። የመምሪያው ምክትል ኀላፊ ልዑል ብርሃን ክትባቱን ለመስጠት ለጤና ባለሙያዎች እና ለሚመለከታቸው አካላት እስከ ወረዳ በተዋረድ ግንዛቤ የማስጨበጥ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እንደተከናወነ አስታውሰው
የተወሰኑ የጸጥታ ችግር ካለባቸው ወረዳዎች በስተቀር በዞኑ ባሉ ኹሉም ከተማ እና ወረዳዎች ክትባቱ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዞኑ ግብዓቶችን በማሟላት እና ወደሚፈለግበት ወረዳ በወቅቱ በማሰራጨት በተመደበለት ጊዜ ክትባት የመስጠት ሥራው እንደተጀመረ ነው የገለጹ፡፡
ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ ቤት ለቤት በመሔድ እና በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ተቋም በመሰጠት ላይ ነዉ ፡፡ከ40 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ልጃገረዶች ክትባቱ እንደሚሰጥም ተገልጿል።
ከኅዳር 09/2017 ዓ.ም እስከ ኅዳር 13/2017 ዓ.ም ድረስ ከዘጠኝ ዓመት እስከ አስራ አራት ዓመት ያሉ ልጃገረዶችን ለማስከተብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
