የደብረ ማርቆስ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ጥገና ሥራ ተጀመረ።

54

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የአስፓልት ጥገና ሥራ እየተካሄደ ነው፤ የአስፋልት ጥገና ሥራውም በኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር እየተሠራ ይገኛል ።

በከተማዋ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የአስፋልት መንገዶች ለተሽከርካሪ ምቹ ባለመሆናቸው በአሽከርካሪዎችና በማኅበረሰቡ ተጠግነው ምቹ እንዲሆኑ በተፈጠሩ የሕዝብ መድረኮች ጥያቄዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል።

ይህንን የማኅበረሰብ ጥያቄ ለመፍታት አሁን በከተማዋ ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም የአስፓልት ጥገና ሥራው ተጀምሯል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት ተጀምረው የተቋረጡ የፌደራልና የክልል ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ እንዲሁም የተጀመሩት በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማኅበረሰቡ ለሰላም ቅድሚያ ሰጦ ሊሠራ እንደሚገባል ከተማ አሥተዳደሩ አሳስቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጸጥታውን እያስከበርን ልማቱን አጠናክረን አስቀጥለናል” የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር
Next article”የሰላምን ጥቅም የምታውቁ ሁሉ ልጆቻችሁን ምከሩ” ብርጋዴር ጄኔራል መለስ መንግስቴ