መሬትን አጥረው በሚገኙ ባለሃብቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

66

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛው ዙር ምርጫ 12ኛው ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎውን እያካሄደ ነው።

በዛሬው ጉባኤ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የ2017 ዓ.ም ዕቅድን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ለልማት የተሰጣቸውን መሬት አጥረው የሚገኙ 41 ባለሃብቶች መሬታቸው ተነጥቋል።

25 ከሚደርሱ ባለሃብቶች ጋርም የተሰጣቸውን መሬት ጥቅም ላይ እንዲያውሉት ከተማ አሥተዳደሩ እየተነጋገረ ነው ብለዋል፡፡

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እነዚህ ባለሃብቶች የተሰጣቸውን መሬት በወቅቱ ለታለመለት ዓላማ የማያውሉት ከኾነ በተጠና ኹኔታ የሚወሰደው ርምጃ በ2017 ዓ.ም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ52 ሺህ በላይ ልጃገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ክትባት እንደሚወስዱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።
Next articleየፈተና ውጤት ማሳወቅ