ከ52 ሺህ በላይ ልጃገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ክትባት እንደሚወስዱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።

32

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማህጸን በር ካንሰርን ቀድሞ ለመከላከል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ከ5 ሺህ በላይ ልጃገረዶችን መከተብ ተችሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ ጅብሪል መርሻ በዞኑ ለ52 ሺህ 300 ልጃገረዶች ክትባቱ እንደሚሠጥ ገልጸዋል።

ከኅዳር 09 እስከ 13/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ክትባቱን ለመስጠት እንደ ክልል ቢታቀድም ዞኑ ካለው መልክዓ ምድር አኳያ እና በተለያዩ ምክንያቶች መጀመር የተቻለው ከኅዳር 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ክትባቱ በተጀመረበት ቀን ብቻም 5 ሺህ 133 ልጃገረዶችን መከተብ ተችሏል።

ክትባቱ በዞኑ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች እንደሚሠጥም ተገልጿል። በዞኑ በቂ ክትባት በመቅረቡ እስከ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተሠራ መኾኑን ነው ያብራሩት።

ክትባቱ ከትምህርት ቤቶች በተጨማሪ በጤና ተቋማት እና ቤት ለቤት ጭምር እንደሚሰጥ ኀላፊው ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በጎንደር ከተማ የዓባይ ጋርመንት ፋብሪካን እየጎበኙ ነው።
Next articleመሬትን አጥረው በሚገኙ ባለሃብቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡